=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
የሌሎችን ስብዕና አትላበስ በውስጣቸውም አትሟሟ። ዘውታሪ ስቃይም ይኸው ነው። ራሳቸውን ፣ ድምፃቸውን እንቅስቃሴያቸውን ፣ ንግግራቸውን ፣ ችሎታቸውንና ነባራዊ ሁኔታዎችን ረስተው በሌሎች ሰዎች ስብዕና ውስጥ የሚቀልጡት ብዙ ናቸው። በዚህም ምክኒያት ያለአቅም መንጠራራት ፣ ያልሆኑትን ነኝ ማለትና መቃጠል ይከተላል ፤ የማንነትና የስብዕና ግድያም ይፈፀማል። ከአባታችን አደም ጀምሮ እስከ መጨረሻው ፍጡር ያሉ ሰዎች ውስጥ ሁለት ሙሉ በሙሉ ተመሳሳይ የሆነ መልክ ያላቸው ሁለት ሰዎች ሊኖሩ አልቻሉም ታዲያ እንዴት በዝንባሌና በባህሪይ ሊገጣጠሙ ይከጅላሉ። አንተ በታሪክ ውስጥ አምሳያ ያልተገኘልህና ወደፊትም በዱንያ ውስጥ አምሳያ የማይኖርህ ልዩ ነህ። አንተ ከዘይድና ከዐምር ሙሉ በሙሉ ትለያለህ። ታዲያ ለምን ራስህን በመመሳሰልና በሌላው ስብዕና ውስጥ ታቀልጠዋለህ? እንደራስ አካላዊ ቅርፅና አኴኋን ሆነህ ኑር።
አል-ቁርአን 2:60
«ሰዎች ሁሉ መጠጫቸውን በእርግጥ አወቁ።»
አል-ቁርአን 2:148
«ለሁሉም የሚዞሩበት አቅጣጫ አላቸው ፤ ወደ መልካም ስራዎችም ተሽቀዳደሙ።»
እንደተፈጠርከው ኑር። ድምፅህን አትቀይር ፤ ቅላፄህን አታበላሽ ፤ አረማመድህን አትቃረን ፤ ነፍስህን በወሕዩ ቁርአን አንፃት ፤ መኖርህን አትሰርዝ ፤ ነፃነትህንም አትግደል። አንተ የተለየ ጣዕምና ቀለም አለህ። እናም አንተን በዚሁ ለዛህና መልክህ እንፈልግሃለን። ምክኒያቱም እንዲሁ ተፈጥረሃል እንዲሁም አውቀንሃል «አንዳችሁ እም-መዓ አይሁን»።
የሰወች አፈጣጠር ከዛፎች አፈጣጠር ጋር ይመሳሰላል። ጣፋጭ እና መራራ ፤ ረዥምና አጭር ስለዚህ ባሉበት ይሁኑ። እንደ ሙዝተክል ከሆንክ ወደ ኮባ ተክልነት ለመቀየር አትጣር ፤ ምክኒያቱም ውበትህና ደረጃህ ሙዝ ነውና የቀለማችን ፣ የቇንቇችንና የዝንባሌያችን እንዲሁም የችሎታችን መለያየት ከፈጣሪ ተዓምራዊ ምልክቶች ውስጥ ይጠቀሳሉና አትጣሳቸው።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|